ብዙነሽ በቀለና ስለሺ ስህን በኔዘርላንድስ የተካሄደውን የ15 ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸነፉ
አዲስ አበባ, ህዳር 9 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - በኔዘርላንድስ ኒጀመገን ከተማ ትናንት በተካሄደው የ15 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ብዙነሽ በቀለና ስለሺ ስህን ማሸነፋቸውን ዓለም አቀፍ አማተር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገለጸ፡፡
ፌዴሬሽኑ በድረ ገጹ ባሰራጨው መረጃ እንዳመለከተው በውድድሩ አትሌት ብዙነሽ በተደጋጋሚ የዓለምን ክብረ ወሰን የያዘችውንና ኔዘርላንዳዊቷ ሎርናህ ኪፕላጋትን በማሸነፍ አድናቆት አትርፋለች፡፡
አትሌቶቹ ዋንኛዋ ተፎካካሪያቸው ሮዝ ቼሪዮትን ስድስት ኪሎ ሜትር ገደማ ጥለዋት መሄዳቸውን አመልክቶ በመጨረሻዎቹ 300ሜትር ላይ ለመሸናነፍ በተደረገው ጥረት ኪፕላጋት ሳይሳካላት መቅረቱን አስታውቋል፡፡
ኪፕላጋት ከውድድሩ በኋላ''ዛሬ እንደ ሌላው ቀን አይደለም፡፡ስጀምር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡ከዚያም በላይ ራሴን ላስጨንቀው አልፈለግኩም፡፡የምሮጥበትም ቦታ መጀመሪያ ጭንቅንቅ ያለ ነበር''ብላለች፡፡
በውድደሩ ብዙነሽ በ47 ደቂቃ ከ36ሰከንድ፣ኪፕላጋት በአንድ ሰከንድ ፣ ሁለተኛዋ ሮዝ ደግሞ በ48 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ ሦስተኛ መውጣቷን ድረ ገጹ ገልጿል፡፡
በወንዶች በተደረገው ውድድር ደግሞ ስለሺ ስህን ከሁለተኛው ኪሎ ሜትር ጀምሮ በመምራት ላይ ከነበረው ቡድን ጋር ሆኖ ሲመራ መቆየቱንና በመጨረሻም ለድል መብቃቱን ዘግቧል፡፡
ስለሺ ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ በሰጠው አስተያየት የውድደሩን ክብረ ወሰን ለመስበር እንደማይችል ገና አምስት ኪሎ ሜትር እንደሮጡ መረዳቱን ድረ ገጹ አመልክቷል፡፡
ስለሺ ውድድሩን 42 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ አንደኛ ሆኖ ሲገባ፣እሸቱ ወንድሙ በ42ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ሁለተኛ ፣ኬንያዊው በርናንድ ኪፕዮጎ በ43 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ሦስተኛ ሆኗል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment